የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ​

ጥቅምት 28, 2023

🇪🇹 ©️ የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማህበር 🇪🇹 ©️ 👇

የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ

የሀገሪቱ የቅጅና ተዛማጅ ኢንዱስትሪ ሕግና ሥርዓትን በተከተለ መልኩ እንዲጎለብት ማድረግ እና የባለመብቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤

ኢትዮጵያ የአዕምሯዊ ንብረት መብቶችን በህግና በስርዓት ለመምራት ስራ ላይ ካዋለቻቸው ህጎች አንደኛው የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ ነው፡፡ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጋር በተያያዘ በአለም ላይ በየጊዜው አዳዲስ እድገቶችና መሻሻሎች ይታያሉ፡፡ በሀገራችንም የቅጅና ተዛማጅ ኢንዱስትሪውና ተያያዥ የስራ ዘርፎች በከፍተኛ ፍጥነት እያደጉ መሆኑና ባለመብቶችም ወቅቱን የጠበቀ የህግና የአሰራር ስርዓት እንዲኖር ካላቸው ፍላጎት አንጻር በሚያደርጉት ግፊት ይህንን ህግ ስራ ላይ ማዋል ችላለች፡፡ ይህ አዋጅ ስራ ላይ ከዋለ በኋላም የባለመብቶች ጥያቄ እያደገ በመምጣቱና በሌሎች የአለም ክፍሎችም አዳዲስ አሰራሮች በመምጣታቸው ምክንያት እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡…

የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ አላማ

የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ የወጣው ሀምሌ፣ 1996 ዓ.ም ሲሆን በሰባት ክፍሎችና በ 40 አንቀጾች የተከፋፈለ ነው፡፡ በመግቢያው ላይ እንደተጠቀሰው አዋጁ የወጣው ሁለት መሰረታዊ አላማዎችን ለማሳካት ታስቦ ነው፡፡ እነዚህም መሰረታዊ አላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ የስነ-ጽሁፍ፣ የኪነ ጥበብና እና ተመሳሳይ የፈጠራ ስራዎች የአንድ ሀገር ባህላዊ/Cultural/፣ ማህበራዊ/Social/፣ ኢኮኖሚያዊ/Economic/፣ ሳይንሳዊ/Scientific/ እና ቴክኖሎጂያዊ ልማትን በማፋጠን ረገድ ትልቁ ሚና የሚጫወቱ በመሆናቸው የሚበረታቱበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የስነጽሁፍ፣ የኪነ ጥበብና እና ተመሳሳይ የፈጠራ ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ በሚከናወኑ ስራዎች ላይ ተዛማጅ መብቶችን በህግ እውቅና መስጠትና ጥበቃ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ይላል፡፡