02. የቅጅ መብት ለማግኘት የሚጠየቁ መመዘኛዎች
nty
ሰኔ 29, 2023
የቅጅ መብት ለማግኘት ቢያንስ የሚከተሉትን መመዘኛዎች ማሟላት ይገባል፡፡
1. የስራው ግዙፍነት ማግኘት/the Work Must be Reduced to Material Form/
በቅጅ መብት ጥበቃ የሚያገኘው ሀሳቡ የተገለጸበት መንገድ እንጂ ሀሳብ ጥበቃ አያገኝም፡፡ ስለዚህ ማንም የፈጠራ ሰው በአዕምሮው ወይም በውስጡ ያለውን ሀሳብ በፅሁፍ ወይም በሌላ ጥበብ ወደ ግዙፍነት ከቀየረው በቅጅ መብት ህግ ጥበቃ ያገኛል፡፡
2. የስራው ወጥነት/Original/
ጥበቃ የሚደረግላቸው ስራዎች ወጥ ስራዎች ማለትም የመጀመሪያ ስራዎች ወይም በወጥ ስራ ላይ ተመስርተው የተሰሩ ሌሎች የፈጠራ ሥራዎች ናቸው፡፡ የስራው ወጥነት ወይም የመጀመሪያ ስራ ሲባል ስራው የተለየ/Unique/ ወይም ፍጹም/Novel/ ማለት ሳይሆን የሌሎችን ስራ በማመሳሰል ወይም በመቅዳት ያልተሰራ ማለት ነው፡፡ በእንግሊዝኛው “the work must be novel or unique but the work must not be a mere or slavish copy of another work.” ይህ ማለት የፈጠራ ሰራተኛው ስራውን የሰራው በራሱ ችሎታ/Skill/ እና ጥረት/Effort/ መሆን አለበት ነው፡፡
Suggestions
ጥበቃ ለማግኘት የሚያስፈልጉ መመዘኛዎች
ህዳር 3, 2023
አስተያየቶች የሉም
በኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ 410/96 እና 872/2007 መሰረት ቃላቶቹ ያላቸው ትርጉም
ህዳር 3, 2023
አስተያየቶች የሉም
ተጠቃሚዎቻችን
ጥቅምት 31, 2023
አስተያየቶች የሉም
የሮያሊቲ ክፍያዎች እንዴት ይተገበራሉ
ጥቅምት 30, 2023
አስተያየቶች የሉም
የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ
ጥቅምት 28, 2023
አስተያየቶች የሉም