03. ተዛማጅ መብት

የተዛማጅ መብቶች የሚነሱት የቅጅ መብት በሚያስገኙ ስራዎች ላይ ሲሆን የቅጅ መብት የሚያስገኙ ስራዎች በህዝብ ዘንድ እንዲታወቁ ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ በአብዛኛው ጊዜ የሚታየው የግንዛቤ እጥረት ችግር የተዛማጅ መብት የሚያስገኙ ስራዎችን የቅጅ መብት እንዳላቸው ተደርጎ መታየት ነው፡፡ ይሁን እንጂ የቅጅ መብት የሚያስገኙ ስራዎች የተዛማጅ መብት ከሚያስገኙ ስራዎች ጋር ይለያያሉ፡፡

ምንም እንኳ የተዛማጅ መብት የሚያስገኙ ስራዎች መሰረት የሚያደርጉት የቅጅ መብት የሚያስገኙ ስራዎችን ቢሆንም፡፡ ለምሳሌ፡- አንድ በመድረክ የቀረበ ቲያትርን እንደ ምሳሌ ብንመለከት፤ በቲያትር መልክ የቀረበው ጽሁፍ የቅጅ መብት ሲኖረው፤ መድረክ ላይ ያቀረቡት ከዋኞች ደግሞ የተዛማጅ መብት ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም ይህ ቲያትር ተቀርጾ ለገበያ ቢቀርብ ሁሉም እንደየመብታቸው ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡

ተዛማጅ መብቶች ማለት ከዋኞች፣ የድምጽ ሪከርዲንግና ፕሮዲዩሰሮች እንዲሁም የብሮድካስቲንግ ድርጅቶች በስራዎቻቸው ላይ ያላቸው መብቶች ማለት ነው፡፡ በአጠቃላይ የተዛማጅ መብት ከአዕምሯዊ ንብረት አይነቶች አንዱ ነው፡፡