እንኳን ወደ CNCM የምዝገባ ገጽ በደህና መጡ
ለሮያሊቲ ይመዝገቡ
በቀላሉ መብትን ማስተዳደር፡ ለግለሰብ ፈጣሪዎች እና የቅጂ መብት ባለቤቶች መብቶቻቸውን ማስተዳደር ከባድ እና ጊዜ የሚወስድ ስራ ነው። የፈቃድ ስምምነቶችን መደራደር፣ የስራዎቻቸውን አጠቃቀም መከታተል ወይም የሮያሊቲ ክፍያ መሰብሰብ ላይችሉ ይችላሉ። መብቶችን ለማስተዳደር፣ ፍቃድ ለመስጠት፣ የሮያሊቲ ክፍያን ለመሰብሰብ እና ለመብት ባለቤቶች ክፍያዎችን ለማከፋፈል የተማከለ አሰራርን እናቀርባለን።
ገቢን መጨመር: ለቅጂ መብት ለተያዙ ስራዎች ስምምነቶችን በማድረግና ክፍያዎችን በመሰብሰብ ገቢዎን ከፍ እናደርጋለን።
ሰፊ ውክልና፡ ከተለያዩ መስኮች እና ዘውጎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ፈጣሪዎችን እና የመብት ባለቤቶችን እንወክላለን። ይህ ሰፊ የፈቃድ አሰጣጥ የሚጠቀሙ ድርጅቶችን ለማግኘት እድሎችን ይሰጥዎታል። የፈቃድ መስጫ ስምምነቶችን ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር ማለትም የቲቪ አና የሬዲዮ ጣቢያዎች፣ ፣ሆቴሎች፣ባር ና ሬስቱራንት፣የስፓርት ቤቶች፣ኮንሰሰርት አዘጋጆች ና የመሳሰሉት
የህግ ጥበቃ እና ጥብቅና፡ CNCM የህግ ከለላ እና ጥብቅና ለፈጣሪዎች እና ለመብት ባለቤቶች ይሰጣል። የቅጂ መብት የተጠበቁ ስራዎችን አጠቃቀም እንከታተላለን፣ ያልተፈቀደ አጠቃቀም ሁኔታዎችን ለይተን እና የቅጂ እና የተዛማጅ መብቶችን ለማስከበር ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን። ድርጅታችን የቅጂ እና የተዛማጅ መብቶች ጥቅምን ይደግፋል።