ማን ነን?

ስለ እኛ

ማህበራችን

የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች የሚያስገኙ ስራዎች ያሏቸው ባለመብቶችን ይወክላል፡፡ እነዚህም ሙዚቀኞች፣ አቀናባሪዎች፣ ደራሲያን፣ ሰዓሊዎች፣ ፎቶግራፍ አንሺዎች፣ ተዋንያን ወዘተ ናቸው፡፡

የቅጅና ተዛማጅ መብት የሚያስገኙ ስራዎች ያሏቸው ባለመብቶች የፈጠራ ስራዎቻቸውን በተሻለ ሁኔታ ለማስተዳደርና የሚደርስባቸውን የመብት ጥሰት ለመከላከል በጋራ መስራታቸው ጠቃሚ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በመሆኑም አገራችን የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ እና በየወቅቱ እያደገ የመጣውን የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ እንቅስቃሴ የሚመጥን የህግ ስርዓት ለመዘርጋት እና ባለመብቶች በተደራጀ እና በተጠናከረ አግባብ መብቶቻቸውን ማስተዳደር የሚችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንዲቻል በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ህገ መንግስት አንቀጽ 55/1 መሰረት በቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 410/1996 እና በአዋጁ ማሻሻያ 872/2007 መሰረት “የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር በ2009 ዓ.ም ተቋቁሟል፡፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 2(32) በተቀመጠው ትርጉም “የጋራ አስተዳደር ማህበር ማለት የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ባለቤቶች መብቶቻቸውን በጋራ ለማስተዳደር የሚያቋቁሙት ማህበር ነው” ይላል፡፡ ስለሆነም በሀገራችን የሚገኙ እና በአምስት ዘርፎች የተሰማሩ በቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ ጥበቃ ሊያገኙ የሚችሉ የፈጠራ ስራ ያሏቸው ባለመብቶች በሰኔ11/2009 ዓ.ም የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር መስርተዋል፡፡

በሀገራችን በኢትዮጵያ የሚገኙ በሙዚቃ፣ በኦዲዮቪዢዋል ወይም ፊልም፣ በስነጽሑፍ፣ በቲያትርና ድራማ እና በስዕልና ቅርጻ ቅርጽ ዘርፎች የፈጠራ ሥራዎች ያሏቸው ባለመብቶች ከሥራዎቻቸው ተገቢውን የኢኮኖሚና የሞራል ጥቅሞች ለማግኘት በቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ መሰረት ያቋቋሙት የጋራ አስተዳደር ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ የአባላት ሥብሥብ በሆነው ጠቅላላ ጉባኤ በተመረጡ አስራ ሶስት የቦርድ አባላት ይመራል፡፡ ቦርዱ ጠቅላላ ጉባኤ በሰጠው ሥልጣንና ሃላፊነት መሰረት ሥራ አስኪያጅ እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞችን ይቀጥራል፡፡ ሥራ አስኪያጁ የጋራ አስተዳደሩን አመታዊ እቅድ እና ሌሎች ተግባራትን በበጀት አስደግፎ በማዘጋጀት በቦርዱ ያጸድቃል፡፡

የቦርድ አባላት

የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር የቦርድ አባላት

የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ከአራት መቶ በሚበልጡ የባለመብቶች ፊርማ የተመሰረተ የጋራ አስተዳደር ሲሆን የአባላት ስብስብን የሚይዝ ጠቅላላ ጉባኤ አለው፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው የጋራ አስተዳደሩ ከፍተኛው የስልጣን ደረጃ ነው፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው የጋራ አስተዳደሩን የሚመሩ የቦርድ አባላትን ይመርጣል፡፡ የቦርድ አባላት ሥራ አስኪያጅና ሌሎች ሰራተኞችን ይቀጥራል፡፡

የኢትዮጵያ የቅጂና ተዛማጅ  መብቶች የጋራ አስተዳደር የቦርድ አባላት ዶ/ር ሙሴ ያዕቆብ (ሰብሳቢ)፣ አርቲስት ቴዎድሮስ ሞሲሳ (ም/ሰብሳቢ)፣ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፣ አርቲስት ደሳለኝ ሃይሉ፣ ወ/ሮ ጸደኒያ ገ/ማርቆስ፣ አርቲስት ጸጋዬ እሸቱ፣ አርቲስት አክሊሉ ኃ/ማርያም፣ አርቲስት ቢንያም ወርቁ፣ አርቲስት ቢንያም አለማየሁ፣ አርቲስት አረገሃኝ ወራሽ፣ አርቲስት ደበሽ ተመስገን፣ አርቲስት አበረ አዳሙ፣ እና አርቲስት ስዩም አያሌው ናቸው፡፡

ዶ/ር ሙሴ ያዕቆብ (ሰብሳቢ)

አርቲስት ቴዎድሮስ ሞሲሳ (ም/ሰብሳቢ)

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ወ/ሮ ጸደኒያ ገ/ማርቆስ

አርቲስት ጸጋዬ እሸቱ

አርቲስት አክሊሉ ኃ/ማርያም

አርቲስት ቢንያም ወርቁ

አርቲስት ቢንያም አለማየሁ

አርቲስት አረጋሃኝ ወራሽ

አርቲስት ደበሽ ተመስገን

አርቲስት አበረ አዳሙ

አርቲስት ስዩም አያሌው

አርቲስት ደሳለኝ ሃይሉ

የሥራ ቡድኖች

በጋራ አስተዳደሩ የቦርድ አባላት የተመረጠው ሥራ አስኪያጅ ከቦርዱ ሃላፊዎች ጋር በጋራ በመሆን በቅጅና ተዛማጅ መብቶች እንዲሁም በሥነ-ጥበብ፣ ኪነ-ጥበብ እና ባህል ጋር በተያያዘ የህግና አስተዳደር ዕውቀት ያላቸውን ብቁ ባለሙያዎች ይቀጥራል፡፡ በተጨማሪም በሒሳብ መዝገብ አያያዝ እውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን በሂሳብ ሰራተኝነት ይቀጥራል፡፡

ማህበራት

የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር በተለያዩ የኪነጥበብ ዘርፎች ማለትም በሙዚቃ፣ ስነ-ጽሁፍ፣ ኦዲዮቪዥዋል፣ ቲያትር እና ድራማ እና ስዕልና ቅርጻ ቅርጽ ዘርፎች የቅጂና ተዛማጅ መብቶች ያሏቸውን ባለቤቶችን በማሰባሰብ የተመሰረተ ማህበር ነው። የጋራ አስተዳደሩ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ማህበር፣ የኢትዮጵያ ፊልም ማህበር፣ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር፣ የኢትዮጵያ ሰዓሊያንና ቀራጺያን ማህበር ወዘተ በአባልነት ይዟል፡፡

አጋሮቻችን