እንዴት ነው ምንሰራው

ሥራዎቻችን

ማን ነን?

የኢትዮጵያ የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር (CNCM) የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች ያሏቸው የፈጠራ ሥራ ባለቤቶች ማለትም ደራሲዎች ፣ ሙዚቀኞች ፣ አቀናባሪዎች ፣ ሰዓሊያን፣ ቀራጺያን፣ ፎቶግራፍ አንሺዎች ወዘተ በመሰባሰብ ስራዎቻቸውን በውክልና እንዲያስተዳድር የመሰረቱት የጋራ ማህበር ነው። ማህበራችን ሰኔ 11 ቀን 2009 የተመሰረተ ሲሆን በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ተመዝግቧል፡፡

ተልዕኳችን

ባለመብቶችን፣ ህግ አውጪውን፣ ህግ ተርጓሚውን፣ ህግ አስፈጻሚውን፣ የሚዲያ ቤተሰቦችን እና አጠቃላይ ማህበረሰቡን ስለ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች ግንዛቤ መፍጠር እና ለውጥ ማምጣት፡፡

ያልተፈቀደ አጠቃቀምን በመከታተል እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እርምጃ በመውሰድ የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች ባለቤቶችን ኢኮኖሚያዊ እና ሞራላዊ መብቶች እናስጠብቃለን።

ባለመብቶችን ወክለን የፈጠራ ሥራዎችን ለንግድ ስራዎቻቸው ለሚጠቀሙ አካላት የፍቃድ ውል እንሰጣለን፡፡

ከጋራ አስተዳደሩ ጋር በገቡት ውል መሰረት የፈጠራ ሥራዎችን ለንግድ ስራዎቻቸው ከተጠቀሙ አካላት የሮያሊቲ ክፍያ እንሰበስባለን፡፡

የፈጠራ ስራዎቻቸው ጥቅም ላይ ውለው የሮያሊቲ ክፍያ ላገኙ ባለመብቶች በድርሻቸው መሰረት እናከፋፍላለን፡፡

አገልግሎቶቻችን

የፈጠራ ሥራ መብት አስተዳደርን ማቃለል

የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች ባለቤቶች መብቶቻቸውን በግል ማስተዳደር ውስብስብ እና ጊዜ የሚወስድ ሊሆን ይችላል። ስለሆነም የጋራ አስተዳደሩ ባለመብቶችን ወክሎ መብቶችን በማስተዳደር፣ የሮያሊቲ ክፍያን በመሰብሰብ እና የተሰበሰበን የሮያሊቲ ክፍያዎች ለማለመብቶች በማከፋፈል ሥራቸውን እናቀላለን።

የፈጠራ ሥራ ባለቤቶችን መብቶች ማስጠበቅ!

የአባሎቻችንን የፈጠራ ስራዎች አጠቃቀም እንከታተላለን፡፡ ያለህጋዊ ፍቃድ የሚጠቀሙና መብት የሚጥሱ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት እንሰራለን። የአባላቶቻችንንም መብቶች እናስከብራለን፡፡

የመጠቀም ፍቃድ ውል ስምምነትን እንሰጣለን

የፍቃድ አሰጣጥ ሂደቱን በማቅለል እና ለተጠቃሚዎች የቅጂ መብት ያላቸውን ስራዎች ለንግድ ሥራዎቻቸው እንዲጠቀሙ የፍቃድ ውል ስምምነቶችን እንሰጣለን፡፡

ትክክለኛ የሮያሊቲ ስርዓት መዘርጋት

የፍቃድ ውል ወስደው ለስራዎቻቸው ከተጠቀሙ አካላት የሮያሊቲ ክፍያዎችን በመሰብስብ ለባለመብቶች ማከፋፈል። ይህም የፈጠራ መብት ባለቤቶች ሥራቸው ጥቅም ላይ ሲውል ተገቢውን ክፍያ ማግኘት እንዲችሉ እና ለአዳዲስ ፈጠራዎች እንዲተጉ ማበረታታት።

ክትትል እና ማስፈጸም

የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ እና ህጎች ጥበቃ ያላቸው ስራዎችን ያለፍቃድ ውል ለንግድ ስራዎቻቸው ጥቅም ላይ የሚያውሉትን በመከታተል እናስቆማለን፡፡ በአጥፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እናደርጋለን። ይህም የፈጠራ ባለቤቶችን መብት ለመጠበቅ እና ለተጨማሪ ሥራ እንዲነሳሱ ይረዳል። የጥበብ ኢንዱስትሪውም እንዲለወጥ ያግዛል፡፡

የፍቃድ ውል ስምምነት እና የሚገኙ ፍቃዶች

የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ያሏቸውን ሥራዎች ለንግድ አገልግሎት የሚያውሉ ተጠቃሚዎች የፍቃድ ውል እንዲያገኙ ምቹ መደላድሎችን ፈጥረናል፡፡ ይኸውም ደረጃውን የጠበቀ የፈቃድ ስምምነት፣ የፍቃድ ውሎች ማደራደር እና የቅጂ መብት ህጎችን ለማክበር ድጋፍ መስጠትን ያካትታል።

ትምህርት እና ስልጠና

በቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች ህጎች፣አሰራሮች እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ትምህርት እና ስልጠና ለአባሎቻችን እና ለፈጠራ ስራ ተጠቃሚዎች፣ ለመንግስት ሃላፊዎችና ሌሎች ለሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤያቸውን ለማሳደግ ትምህርተና ስልጠና እንሰጣለን፡፡

ተሟጋችነት እና ውክልና

በሚገኙ የመንግስትና የግል መድረኮች የፈጠራ ባለቤቶች መብቶቻቸው እንዲከበርና ከሥራዎቻቸው ተገቢውን ጥቅም ማግኘት እንዲችሉ እንሞግታለን፡፡ የፈጠራ ባለቤቱን ወክለን ያለመታከት እንሰራን፡፡ የሚመለከታቸውን የመንግስት ሃላፊዎችና ሰራተኞች ዘርፉን እንዲያግዙ እና በጎ ተጽዕኖ እንዲያሳርፉ እንወተውታለን፡፡

የፈጠራ ስራዎችን መደገፍ

የፈጠራ ስራዎችን እድገት እና ልማት ለማፋጠን እንዲሁም ባለመብቶች ስራዎቻቸው በህዝብ ዘንድ እንዲታወቁ የማስተዋወቅ ስራዎችን እንሰራለን፡፡ በተጨማሪም የፈጠራ ፕሮጄክቶች ሥራ ላይ እንዲውሉ፣የግብይት፣ የማስተዋወቂያ ፣ የስርጭት እና ፍቃድ አሰጣጥ ድጋፍ እንዲያገኙ ያመቻቻል።

ምንን እንወክላለን?

የጋራ አስተዳደር ማህበሩ የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች ባለቤቶችን ይወክላል፡፡ እነዚህም ደራሲያን፣ ሙዚቀኞች፣ አቀናባሪዎች፣ ተዋናዮች፣ ሰዓሊዎች፣ ፎቶግራፍ አንሺዎች ወዘተ ናቸው፡፡

ማህበራችን በሚከተሉት የቅጅና ተዛማጅ መብቶች በሚያስገኙ ሥራዎች ላይ ይሠራል፡፡

ሙዚቃ

ቲያትር እና ድራማ

ስነ-ጽሁፍ

ኦዲዮ ቪዥዋል እና ፊልም

ፎቶግራፍ ማንሳት

በፈጠራ ስራዎችዎ የሮያሊቲ ክፍያ ያግኙ!

ፈቃድ ለምን ያስፈልግዎታል?

በኢትዮጵያ የአዕምሯዊ ንብረት ህግ መሰረት የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች የሚስገኙ ስራዎችን ያለባለቤቱ ፍቃድ ማባዛት እና ማሰራጨት አይቻልም። ያለውል እና ህጋዊ ፈቃድ መጠቀም በቅጂ መብት ጥሰት ምክንያት የፍትሐ ብሔር እና የወንጀል ተጠያቂነት ያስከትላል፡፡ የቅጅ መብት መጣስ በቅጅና ተዛማጅ መብት ጥበቃ አዋጅ 410/1996 አንቀጽ 34 እና 36 መሰረት የፍታብሄርና የወንጀል ቅጣት ያስከትላል፡፡

ማን የፍቃድ ውል ያስፈልገዋል?

ድርጅቶች

የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የሚስገኙ የፈጠራ ሥራዎችን ለንግድ ሥራዎቻው ለመጠቀም የፍቃድ ውል የሚያስፈልጋቸው የሬዲዮ ጣቢያዎች፣ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች እና ኔትወርኮች፣ ኮንሰርት አዘጋጆች፣ ባር እና ሬስቶራንቶች፣ የምሽት ክለቦች፣ ሆቴሎች፣ ጂሞች እና ስፖርት ቤቶች፣ የሙዚቃ ዥረት አገልግሎት አቅራቢዎች እና ደንበኞቻቸውን ለማዝናናት እና ለመሳብ የፈጠራ ስራዎችን የሚጠቀሙ ድርጅቶች በሙሉ የፍቃድ ውል ስምምነት መውሰድ እና ተገቢውን የሮያሊቲ ክፍያ መክፈል አለባቸው።

የፈጠራ ሥራን ለንግድ ሥራዎቻቸው ለሚጠቀሙ ለተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ፈቃድ እንሰጣለን

ቡና ቤቶች እና የምሽት ክለቦች

ሆቴሎች እና ሪዞርቶች

የጤና እና የአካል ብቃት ማሰልጠኛ ተቋማት

ምግብ ቤቶች

የችርቻሮ መደብሮች

ድረገጾች እና መተግበሪያዎች

የፈጠራ ስራዎችን በነጻነት እና በህጋዊ መንገድ ለንግድ ሥራዎ እንዲጠቀሙ ያስችልዎታል፡፡ የፈጠራ ባለቤቶችን ድካም ያለአግባብ ከመመዝበር ይታደግዎታል፡፡

የምንሠራቸው ሥራዎች...

ምዝገባ

የፈጠራ ስራ ባለመብቶች የባለቤትነት መብቶቻቸውን ለማስከበርና ከሥራዎቻቸው ተገቢውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያገኙ ዘንድ በጋራ አስተዳደር ማህበሩ ስርዓት ውስጥ ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡

ፍቃድ መስጠት

የቅጂ እና ተዛማጅ መብት ያላቸውን ሥራዎች ለንግድ አገልግሎት ለሚጠቀሙ ድርጅቶች እና ተቋማት የጋራ አስተዳደሩ የመጠቀም ፍቃድ ውል ስምምነት ይሰጣል፡፡

ተቆጣጣሪነት

የቅጅና ተዛማጅ መብት የሚስገኙ ሥራዎችን ያለፍቃድ ውል ስምምነት ለንግድ ሥራዎቻቸው የሚጠቀሙ ድርጅቶችን በመከታተል ለህግ ያቀርባል፡፡ የአባላቱን መብት ያስከብራል፡፡

ሮያሊቲ መሰብሰብ

የቅጂ እና ተዛማጅ መብት ያለው ስራ ጥቅም ላይ ሲውል የጋራ አስተዳደሩ ባለመብቶችን ወክሎ የሮያሊቲ ክፍያ ይሰበስባል፡፡

የሮያሊቲዎችን አሰራጭ

በፍቃድ ውል ስምምነት መሰረት የተሰበሰበን የሮያሊቲ ክፍያ ለባለመብተቹ እንደ ድርሻቸው በመቶኛ ያከፋፍላል።

አጋሮቻችን