05. በቅጂ መብት ጥበቃ የሚያገኙ ስራዎች
nty
ሰኔ 29, 2023
እንደማንኛውም የአዕምሯዊ ንብረት ህግ የቅጅ መብት ህግ/Copyright law/ የፈጠራ ባለቤቶችን መብት በመጠበቅ ፈጠራን ያበራታታል፡፡ የቅጅ መብት ሰዎች በስነ-ፅሁፍ/Literary/ና ስነ-ጥበብ/Artistic/ ስራዎች ላይ ያላቸውን የአዕምሮ ውጤት ነው፡፡ ስለሆነም የቅጅ መብት የሚገባቸው ዋናዎቹም ስራዎች የስነ-ፅሁፍና የስነ-ጥበብ ውጤቶች ናቸው፡፡ እነዚህም ጽሁፍ፣ ሙዚቃ፣ ልዩ ጥበብ ስራ እንደ ቀለም ቅብ ፣ ቅርጻ ቅርጽ እና ቴክኖሎጂን መሰረት ተደርጎ የተሰሩ ስራዎች ለምሳሌ፡-የኮምፒዩተር ፕሮግራሞች ና የኤሌክትሮኒክ ዳታ ቤዝ ወዘተ ናቸው፡፡
በቅጂ መብት ጥበቃ የሚያገኙ ስራዎች
የፈጠራ ስራዎች በቅጅ መብት ስር ተገቢው ጥበቃ ይደረግላቸዋል፡፡ በሀገሮች መካከል የቅጅ መብት ህጎችና የህጎቹን አተገባበር አስመልክቶ ጥቃቅን ልዩነቶች ይስተዋላሉ፡፡ ለምሳሌ፡- በፍርድ ቤቶች ውሳኔ አንዳንድ ሀገራት የግል ደብዳቤዎችን/Private lettrs/፣ የፍቺ ማንዋሎችን/Divorce Guide/፣ የጸጉር ቁርጥ/Haircuts/፣ የፈተና ወረቀቶች/Examination Papers/ ወዘተ የቅጅ መብት ጥበቃ ይሰጣሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ በሁሉም ሀገራት ስምምነት ያገኘው አንድ የፈጠራ ስራ እንደስራ ብቃት የሚኖረው ወጥ ወይም የመጀመሪያ ስራ ሲሆንና ስራው ግዝፈት ሲያገኝ ነው፡፡
Suggestions
ጥበቃ ለማግኘት የሚያስፈልጉ መመዘኛዎች
ህዳር 3, 2023
አስተያየቶች የሉም
በኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ 410/96 እና 872/2007 መሰረት ቃላቶቹ ያላቸው ትርጉም
ህዳር 3, 2023
አስተያየቶች የሉም
ተጠቃሚዎቻችን
ጥቅምት 31, 2023
አስተያየቶች የሉም
የሮያሊቲ ክፍያዎች እንዴት ይተገበራሉ
ጥቅምት 30, 2023
አስተያየቶች የሉም
የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ
ጥቅምት 28, 2023
አስተያየቶች የሉም