በኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ 410/96 እና 872/2007 መሰረት ቃላቶቹ ያላቸው ትርጉም

ህዳር 3, 2023

🇪🇹 ©️ የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማህበር 🇪🇹 ©️ 👇

ኦዲዮቪዥዋል ስራ

የኦዲዮቪዥዋል ስራ ማለት ለዚሁ ተግባር በተሰራ መሳሪያ በመጠቀም በቀላሉ ሊታይ የሚችል፣ ተከታታይነትና ተዘማጅነት ያለውን በድምጽ የታጀበ ወይም ያልታጀበ የእንቅስቃሴ ስሜትን የሚፈጥሩ ምስሎችን የያዘ ማንኛውም ስራ ሲሆን ሲኒማቶግራፊና ፊልሞችን ይጨምራል፡፡

ፎቶ ግራፍ ስራ

የፎቶ ግራፍ ስራ ማለት አንድ ምስል ለማውጣት ወይም ምስልን በማናቸውም ዘዴ ለማውጣት እንዲቻል ብርሀን ወይም ሌላ ጨረርን በማናቸውም የመቀበያ አካል ላይ መቅረጽ ሲሆን ፊልምን አይጨምርም፡፡

ድምጽ ሪኮርዲንግ

የድምጽ ሪኮርዲንግ ማለት የክውና ድምጽ ወይም ሌላ ድምጽ ወይም አምሳያ ምትክ ግዝፈት ያገኘበት ዘዴን ወይም ድምጹ የተቀረጸበትን አካል ግምት ውስጥ ሳይገባ ክዋኔ ወይም ድምጽ ወይም አምሳያው ግዙፍነት እንዲያገኝ ማድረግ ሲሆን የኢዲዮቪዥዋል ስራን፣ የድምጽ ትራክን የመሳሰሉ የድምጽና ምስል ገዝፈትን አይጨምርም፡፡

ከዋኝ/Performers/

በአንቀጽ 2(19) እንደቀረበው ከሆነ ከዋኝ/Performers/ ማለት ተዋናይ፣ ዘፋኝ፣ ዘማሪ፣ ሙዚቀኛ፣ ተወዛዋዥ እና ሌላ ማናቸውም የሚተውን፣ የሚያወጣ፣ የሚጫወት፣ የሚዘፍን፣ የሚያዝናና ወይም በሌላ ማናቸውም አኳኋን የስነጽሁፍና የኪነጥበብ ስራን የሚከውን ግለሰብ ነው፡፡

ፕሮዲወሰር

ፕሮዲወሰር ማለት በአንቀጽ 2፡20 እንደተገለጸው የኦዲዮቪዥዋል ስራ ለመስራት ሀሳብ ያመነጨና ስራውን በሀላፊነት የሚሰራ ሰው ነው፡፡

ታተመ ስራ

የታተመ ስራ ማለት የአንድን ስራ ወይም የድምጽ ሪከርዲንግ ተጨባጭነት ያላቸው ቅጂዎች በሽያጭ/Sale/፣ በኪራይ/Rental/፣ ለህዝብ ውሰት/Public Lending/ እንዲሁም የቅጂዎችን ባለቤትነት ወይም ይዞታ ለማስተላለፍ እንደሁኔታው በስራው አመንጪ ወይም በቅጂ ባለመብቱ ወይም በድምጽ ሪኮርዲንግ ፕሮዲውሰር ፈቃደ በበቂ መጠን ለህዝብ የቀረበ ስራ ነው፡፡ (አንቀጽ 2፡22)