በኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ ጥበቃ የሚያገኙ እና የማያገኙ ስራዎች
ህዳር 3, 2023
🇪🇹 ©️ የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማህበር 🇪🇹 ©️ 👇
በኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ ጥበቃ የሚያገኙ እና የማያገኙ ስራዎች
በሀገራችን የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ 410/1996 የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን ጥበቃ ይሰጣል፡፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 2 ቁጥር 8 የቅጅ መብት ማለት ከአንድ ስራ የሚመነጭ የኢኮኖሚ መብት ሲሆን አግባብነት ባለው ጊዜ የሞራል መብቶችን ይጨምራል ይላል፡፡
በተጨማሪ በዚሁ አንቀጽ በቁጥር 14 ላይ የተዛማጅ መብትን ትርጓሜ እንዲህ በማለት ያስቀምጣል ተዛማጅ መብት ማለት ከዋኝ/Performers/፣ የድምጽ ሪኮርዲንግ ፕሮዲውሰር/Producer of Sound Recordings/፣ የብሮድካስቲንግ ድርጅት በስራው ላይ ያለው መብት ነው፡፡ በእነዚህ በሁለት መብቶች ትርጉም ላይ የምናገኛቸው በርካታ ቃላቶች አሉ፡፡
ጥበቃ የሚያገኙ
በአዋጁ አንቀጽ 2 ቁጥር 30 ላይ እንደተዘረዘረው የቅጅ ወይም ተዛማጅ መብት ጥበቃ የሚያገኝ ስራ
ሀ. መጽሀፍ፣ ቡክሌት፣ በመጽሄት ወይም በጋዜጣ ላይ የሚገኝ መጣጥፍ፣ የኮምፒዩተር ፕሮገራም
ለ. ንግግር/Speeches/፣ ሌክቸር፣ ለአንድ በተወሰነ ክፍል የሚደረግ መልእክት አዘል ንግግር፣ የሀይማኖት ስብከት/Sermons/ እና ሌላ በቃል የሚቀርብ ስራ
ሐ. ድራማ፣ ድራማዊ የሙዚቃ ስራ፣ በእንቀስቃሴ ብቻ የሚቀርብ ድራማ/ ፓንቶማይምስ/ የመድረክ ውዝዋዜ እና ሌላ ለመድረክ ተብሎ የሚሰራ ስራ
መ. የሙዚቃ ስራ
ሠ. የኦዲዮቪዥዋል ስራ
ረ. የኪነህንጻ ስራ
ሰ. የስዕል/Drawing/፣ የቅብ/Painting/፣ የሀውልት/Sculpture/፣ የቅርጻ ቅርጽ/Engraving /፣ የህትመት/Lithography/፣ የፊደል ቅርጽ ጥልፍ እና ሌላ የስነ ጥበብ ስራ/Fine Arts/
ሸ. የፎቶ ግራፍ ስራ
ቀ. ስዕላዊ መግለጫ/Illustrations/፣ ካርታ/Maps/፣ ፕላን/Plan/፣ ንድፍ/Sketches/ እና ባለሶስት ገጽታ ከጂኦግራፊ፣ ቶፖግራፊ፣ ስነ ህንጻ ወይም ሳይንስ ጋር የተያያዘ ስራ
እነዚህ በሙሉ የመጀመሪያ ስራዎች ናቸው፡፡ የቅጅና ተዛማጅ መብቶቸ ጥበቃ አዋጅ የመጀመሪያ ስራን መሰረት ያደረገ ስራን/Derivative Works/ ጥበቃ ይሰጣል፡
በአንቀጽ 4 ላይ እንደጠቀምጠው ትርጉም/Translation/፣ የማመሳሰል ስራ/Adaptations/፣ ቅንብር/Arrangements/ እና ሌላ የስራውን አይነት የሚቀየር ወይም የሚያሻሽል ስራ/Other Transformations or Modification of Works/ እና በይዘት፣ በቅንብር ወይም በአመራረጥ የተነሳ ኦርጂናል የሆነና በሚነበብ መሳሪያ ወይም በሌላ መልክ ያለ ኢንሳይክሎፒድያ፣ የቅኔ ስብስብ ወይም ዳታቤዝን የመሳሰለ የስብስብ ስራ እንደ ስራ ጥበቃ ይደረግላቸዋል፡፡
ጥበቃ የሚያገኙ
በተጨማሪ በአዋጁ በአንቀጽ 5 ላይ እንደተገለጸው በአዋጁ አንቀጽ 2፣3 እና 4 ጥበቃ የሚደረግላቸው የመጀመሪያ እና የመጀመሪያ ስራን መሰረት ያደረጉ ስራዎች የተገለጹ ቢሆንም በዚህ አዋጅ ጥበቃ የማይደረግላቸው ስራዎች አሉ፡፡
Suggestions
ጥበቃ ለማግኘት የሚያስፈልጉ መመዘኛዎች
ህዳር 3, 2023
አስተያየቶች የሉም
በኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ 410/96 እና 872/2007 መሰረት ቃላቶቹ ያላቸው ትርጉም
ህዳር 3, 2023
አስተያየቶች የሉም
ተጠቃሚዎቻችን
ጥቅምት 31, 2023
አስተያየቶች የሉም
የሮያሊቲ ክፍያዎች እንዴት ይተገበራሉ
ጥቅምት 30, 2023
አስተያየቶች የሉም
የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ
ጥቅምት 28, 2023
አስተያየቶች የሉም