እኛ ማን ነን?
የኢትዮጵያ የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር
የኢትዮጵያ የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር (CNCM) የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች ያሏቸው የፈጠራ ሥራ ባለቤቶች ማለትም ደራሲዎች ፣ ሙዚቀኞች ፣ አቀናባሪዎች ፣ ሰዓሊያን፣ ቀራጺያን፣ ፎቶግራፍ አንሺዎች ወዘተ በመሰባሰብ ስራዎቻቸውን እንዲያስተዳድር የመሰረቱት የጋራ ማህበር ነው። የጋራ አስተዳደሩም ባለመብቶችን በመወከል ለተጠቃሚዎች የፈቃድ ውል ይሰጣል፣ የሮያሊቲ ክፍያን በመሰብሰብ ለባለመብቶች እንደየድርሻቸው ያከፋፍላል፡፡ በተጨማሪም የመብት ማስከበርን እና የግንዛቤ ማሳደግ ስራን ይሰራል፡፡
የምንሰራባቸው ዘርፎች
ለፈጠራ ስራዎ ተገቢውን ክፍያ ያግኙ!!!
ሙዚቃ
ቲያትር እና ድራማ
ስነ-ጽሁፍ
ኦዲዮ ቪዥዋል እና ፊልም
ስዕል እና ፎቶግራፍ
ለፈጠራ ስራዎ ተገቢውን ክፍያ ያግኙ!!!
ስለ እኛ
ለባለ መብቶች አና ለፈጣሪዎች መብቶቻቸውን ለማስተዳደር ወሳኝ መፍትሄ ነው፡፡ ቀላል እና ምቹ የፈጠራ ስራዎች ምዝገባ ስርዓት፣ጠንካራ ቁጥጥር፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የፍቃድ አሰጣጥ፣ምቹ የክፍያ ስርዓት፣ግልፅ የሆነ ሪፖርት የሚያገኙበት አሰራር ዘርግተናል፡፡ ከጋራ ማህበሩ ጋር በመስራት መብትዎን ያስጠብቁ፣ገቢዎን ከፍ ያድርጉ!
ማን ፈቃድ ያስፈልገዋል?
ለተለያዩ የንግድ ዓይነቶች ፈቃድ እንሰጣለን
ቡና ቤቶች እና የምሽት ክለቦች
ሆቴሎች እና ሪዞርቶች
የጤና እና የአካል ብቃት ማዕከላት
ምግብ ቤቶች
የችርቻሮ መደብሮች
የቲቪና የሬድዮ ጣብያ
የስፖርት ቤቶች
ኮንሰርት አስተዋዋቂ
ትራንስፖርት አቅራቢዎች
የበረራ መዝናኛዎች
የጅምላ አቅራቢዎች
በንግድዎ ውስጥ ያሉ የፈጠራ ስራዎችን በነጸነት እና በህጋዊ መንገድ እንዲጠቀሙ ያስችልዎታል!
የምንሰራቸው ስራዎች
CNCM የጥበብ ማህበረሰቡን ይደግፋል፣ ባለመብቶችን ወክሎይከራከራል እና የሁሉንም አባላት ሥራዎች ያበረታታል።
ይመዝገቡ
የፈጠራ ሥራ ባለቤቶች ከፈጠራ ሥራዎቻቸው ተገቢውን የኢኮኖሚ ጥቅም ማግኘት እንዲችሉ ሥራዎቻቸውን እንመዘግባለን፡፡
ፈቃድ
የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች ያላቸውን ስራዎችን ለንግድ ሥራዎቻቸው በህጋዊ መንገድ ለመጠቀም ለሚፈልጉ ተጠቃሚዎች የፍቃድ ውል ስምምነቶችን ያመቻቻል፡፡
ክትትል
የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ያሏቸው ሥራዎች የት እና መቼ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ በመከታተል ሪፖርት ያደረጋል፡፡
የሮያሊቲ ገንዘብ መሰብሰብ
የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች ያሏቸው ሥራዎች ጥቅም ላይ ሲውሉ የጋራ አስተዳደሩ ባለመብቶችን በመወከል ክፍያ ይሰበስባል፡፡
ሮያልቲ ማከፋፈል
ጥቅም ላይ ከዋሉ የፈጠራ ሥራዎች የተሰበሰበውን ክፍያ ለመብቱ ባለቤቶች እንደየ ድርሻቸው ያከፋፍላል።
መፍትሄዎች እና ጥቅሎች
የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማህበር የጥበብ ማህበረሰቡን ይደግፋል፣ ባለመብቶችን ወክሎ መብቶቻቸውን ለማስከበር ይሰራል እንዲሁም የሁሉንም አባላት ሥራዎች ያበረታታል።
ድጋፍ
አላማችን የቅጂ እና የተዛማጅ መብቶች መከበርን ለማረጋገጥ ከሁሉም ባለድርሻዎች እና ሌሎች ፍላጎት ካላቸው አካላት ጋር መተባበር ነው። የሮያሊቲ ክፍያን ከሁሉም ተጠቃሚዎች በተገቢው መንገድ ለመሰብሰብ እና ለማቀላጠፍ በብቃት እየሰራን እንገኛለን።
ለአባላቶቻችን
በቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ትምህርት እና ስልጠና እና የግንዛቤ ፈጠራ ለአባሎቻችን እና ለተጠቃሚዎች እንሰጣለን፡፡
አጋሮቻችን
እየሰራን ያለነው...
ሁሉንም ማህበረሰብ ለመድረስ ነው!
የሀገራችንን የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ህጎችንና ደንቦችን እንዲሁም በዘርፉ ባለው አለም አቀፍ አሰራር ላይ በቂ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ደረጃ እናንተን ለማገልገል ይሰራሉ፡፡
ብሮሸር ያውርዱ
የምናቀርበውን በዝርዝር ያግኙ፣ እኛ ለጥቅምዎ ቆመናል።