የሮያሊቲ ክፍያዎች እንዴት ይተገበራሉ
ጥቅምት 30, 2023
🇪🇹 ©️ የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማህበር 🇪🇹 ©️ 👇
የየሮያሊቲ ክፍያ ምንድን ነው?
ሮያሊቲ አንድ የጥበብ ስራ ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ ተጠቃሚዎች የሚከፍሉት ክፍያ ነው። ተጠቃሚዎች ለመጠቀም የሚፈልጉትን ስራ ለመጠቀም ፈቃድ ማግኘት አለባቸው። ይህ ፈቃድ ድርጅቶች በቅጂ መብት ስር የተያዙ ስራዎችን የመጠቀም መብት ይሰጣቸዋል።የሮያል ስምምነት በፈቃድ ሰጪው እና በፈቃድ ተጠቃሚው መካከል የሚደረግ የሕግ ውል ነው፣ስምምነቱ የሮያሊቲ ክፍያ ተመንን ፣ ስምምነቱ የተሳተፉትን ወገኖች ፣ የተሰጡ መብቶች ዝርዝር ፣ የአጠቃቀም ጊዜውን፣የሚከፈለውን የክፍያ ውሎች እና መጠን ያሳያል።
የሮያሊቲ ክፍያዎች መቼ ይከፈላሉ?
ሁሉም ድርጅቶች በቅጅ ስራ የተያዙ ስራዎችን ለመጠቀም መክፈል ይጠበቅባቸዋል. እነዚህ ክፍያዎች የሚመጡት ከንግድ ድርጅቶች ወይም የፍቃድ ክፍያዎች ነው። የሮያሊቲ ክፍያ የሚከፈለው አንድ የጥበብ ስራ በይፋ ለህዝብ በሚቀርብበት ጊዜ ነው።
የሮያሊቲ ክፍያዎች እንዴት ይተገበራሉ?
የሮያሊቲ ሥራ አፈጻጸም አጠቃላይ ሂደት በሶስት ደረጃዎች ሊጠቃለል ይችላል፡-
የሮያሊቲ ክፍያ የሚሰበስበው ማነው?
የቅጂ እና ተዛማች መብቶች የጋራ አስተዳደር ማህበር በፈጠራ ስራ ባለቤቶች መሃል እንደ መገናኛ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል። በተጨማሪም አፈጻጸሞችን ይቆጣጠራሉ ፣ ይከታተላሉ፣ የፍቃድ አሰጣጥ ክፍያዎችን ይሰበስባሉ እና ተገቢው የሮያሊቲ ክፍያ ለመብት ባለቤቶች መከፋፈሉን ያረጋግጣሉ።
የሮያሊቲ ክፍያ እንዴት ነው ሚሰበሰበው?
የፈጠራ ስራ ባለቤቶች የ ሮያሊቲ ክፍያ ለማግኘት ማህበሩን መቀላቀል አለባቸው እና ማህበሩ ስራዎቹን ለህዝብ ከሚጠቀሙ ተቋማት እና መድረኮች ጋር የፍቃድ ስምምነቶችን ይፈፅማሉ። በዉሉ መሰረት ማህበሩ የ ሮያሊቲ ክፍያ ከሰበሰበ ቦሃላ ለሚመለከታቸው የመብት ባለቤቶች ያከፋፍላሉ።በተጨማሪም በዓለም ዙሪያ ካሉ የጋራ አስተዳደር ጋር ስምምነት በማድረግ አለም አቀፍ ሮያሊቲዎችን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።
የሮያሊቲ ክፍያ ሚከፍለው ማን ነው?
የሮያሊቲ ክፍያ የሚከፈለው አንድ ስራ ለህዝብ በሚተላለፍበት ጊዜ ነው - በሬዲዮ ወይም በቴሌቪዥን በሚሰራጭ ወይም በምግብ ቤቶች ፣ የስፖርት ቤቶች፣ቡና ቤቶች ወይም በምሽት ክለቦች እንዲሁም በቀጥታ ስርጭት በሚተላለፍበት ጊዜ ነው ስለዚህ እነዚህ ድርጅቶች በቅጂ ስራ ስር የተያዙ ስራዎችን ለንግድ አገልግኢሎት ለመጠቀም ከፈለገ ፍቃድ ማግኘት ይጠበቅበታል።
Suggestions
ጥበቃ ለማግኘት የሚያስፈልጉ መመዘኛዎች
ህዳር 3, 2023
አስተያየቶች የሉም
በኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ 410/96 እና 872/2007 መሰረት ቃላቶቹ ያላቸው ትርጉም
ህዳር 3, 2023
አስተያየቶች የሉም
ተጠቃሚዎቻችን
ጥቅምት 31, 2023
አስተያየቶች የሉም
የሮያሊቲ ክፍያዎች እንዴት ይተገበራሉ
ጥቅምት 30, 2023
አስተያየቶች የሉም
የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ
ጥቅምት 28, 2023
አስተያየቶች የሉም