11. የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ አንዳንድ አንቀጾች
nty
ሰኔ 29, 2023
አንቀጽ 6፡- ጥበቃ ለማግኘት የሚያስፈልጉ መመዘኛዎች / Requirements for Protection /
በሀገራችን የቅጅ ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ መሰረት ጥበቃ ለማግኘት የሚያስፈልጉ መመዘኛዎች ሁለት ሲሆኑ የስራው አመንጪው የስራ አላማና የስራው የጥራት ደረጃ ግምት ውስጥ አይገባም፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 6(1) እንደተገለጸው አንድ የፈጠራ ስራ ጥበቃ የሚያገኘው ስራው ወጥ/Original/ ከሆነ እና ግዙፍነት/Fixed/ ካገኘ ነው፡፡ እነዚህን ሁለት መመዘኛዎች የሚያሟላ የስራ አመንጪ ስራውን በማውጣት ምክንያት ብቻ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጥበቃ ያገኛል፡፡
አንዲሁም ፎቶግራፍ ስራዎች ጥበቃ የሚያገኙት በአንቀጽ 6(1) ከተገለጹት ሁለት መመዘኛዎች (ወጥነትና ግዙፍነት) በተጨማሪ የአንድ ስብስብ አካል ሲሆኑ ወይም በመጽሀፍ መልክ ሲታተሙ፤ ወይም የስራ አመንጪውን ወይም ወኪሉን ስምና አድራሻ ሲይዙ ይሆናል፡፡ (አንቀጽ 6(2))
አንቀጽ 3፡- በኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ ጥበቃ የሚያገኙ እና የማያገኙ ስራዎች
በሀገራችን የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ 410/1996 የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን ጥበቃ ይሰጣል፡፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 2 ቁጥር 8 የቅጅ መብት ማለት ከአንድ ስራ የሚመነጭ የኢኮኖሚ መብት ሲሆን አግባብነት ባለው ጊዜ የሞራል መብቶችን ይጨምራል ይላል፡፡ በተጨማሪ በዚሁ አንቀጽ በቁጥር 14 ላይ የተዛማጅ መብትን ትርጓሜ እንዲህ በማለት ያስቀምጣል ተዛማጅ መብት ማለት ከዋኝ/Performers/፣ የድምጽ ሪኮርዲንግ ፕሮዲውሰር/Producer of Sound Recordings/፣ የብሮድካስቲንግ ድርጅት በስራው ላይ ያለው መብት ነው፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 2 ቁጥር 30 ላይ የቅጅ ወይም ተዛማጅ መብት ጥበቃ የሚያገኝ ስራ ተዘርዝሯል፡፡
Suggestions
ጥበቃ ለማግኘት የሚያስፈልጉ መመዘኛዎች
ህዳር 3, 2023
አስተያየቶች የሉም
በኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ 410/96 እና 872/2007 መሰረት ቃላቶቹ ያላቸው ትርጉም
ህዳር 3, 2023
አስተያየቶች የሉም
ተጠቃሚዎቻችን
ጥቅምት 31, 2023
አስተያየቶች የሉም
የሮያሊቲ ክፍያዎች እንዴት ይተገበራሉ
ጥቅምት 30, 2023
አስተያየቶች የሉም
የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ
ጥቅምት 28, 2023
አስተያየቶች የሉም