09. የኢትዮጵያየቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማኅበር መቋቋም ምክንያቶች?
nty
ሰኔ 29, 2023

የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ማለትም የሥራ አመንጭዎች ፣የከዋኞች፣የድምጽ ሪከርዲንግ ፕሮዲውሰሮች እና የብሮድካስት ድርጅቶች መብቶች በቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 410/96 ጥበቃ የተደረገላቸው ቢሆንም ይህ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ለመብቶች ተገቢውን ጥበቃ ከመስጠት ባለፈ በዋናነት የጋራ የመብት አስተዳደር/የሮያሊቲ ሥርዓት ሳይዘረጋ በመቆየቱ፣
የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማኅበር መቋቋም ምክንያቶች?
የቅጅና ተዛማጅ ባለመብቶች መብቶቻቸውን በመላው ሀገሪቱና በዓለም ዙሪያ ከእያንዳንዱ የስራ ተጠቃሚ ጋር በግል በመገናኘት መብቶቻቸው ለማስተዳደር እጅግ አስቸጋሪ ወይም ፈጽሞ የማይቻል በመሆኑ፣
የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማኅበር በሌለበት ሁኔታ የፈጠራ ሥራ ተጠቃሚዎች አንድን የፈጠራ ሥራ ለመጠቀም በሚፈልጉበት ጊዜ እያንዳንዱን የፈጠራ ባለመብት በግል ለማግኘትና ለማስፈቀድ በጣም አስቸጋሪ በመሆኑ፣
በየወቅቱ እያደገ የመጣውን ቴክኖሎጂና ከዚህ ጋር ተያይዞ የመጣውን የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ እንቅስቃሴ የሚመጥን የሕግ ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ፣
የፈጠራ ስራ ባለሙያዎች በተናጠል መብቶቻቸውን ለማስተዳደር የሚያባክኑትን ገንዘብ ጊዜና እምቅ የፈጠራ ችሎታ ተጠቅመው አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን ለማመንጨት ይችሉ ዘንድ መብቶቻቸዉን በተደራጀ ሁኔታ የሚያስተዳድርላቸው የጋራ አስተዳደር ማህበር መመስረት አስፈላጊ በመሆኑ፣
የቅጅና ተዛማጅ መብት ባለመብቶች በሕግ የተሰጣቸውን መብቶቻቸውን በጋራ ማስተዳደር የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እንዲቻል፣
ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማኅበር በአዋጅ 410/1996 እና በአዋጅ ማሻሻያ አዋጅ 872/2007 መሰረት የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የሚያስገኙ ስራዎችን ለማስተዳደር ተቋቁሟል፡፡
Suggestions
ጥበቃ ለማግኘት የሚያስፈልጉ መመዘኛዎች
ህዳር 3, 2023
አስተያየቶች የሉም
በኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ 410/96 እና 872/2007 መሰረት ቃላቶቹ ያላቸው ትርጉም
ህዳር 3, 2023
አስተያየቶች የሉም
ተጠቃሚዎቻችን
ጥቅምት 31, 2023
አስተያየቶች የሉም
የሮያሊቲ ክፍያዎች እንዴት ይተገበራሉ
ጥቅምት 30, 2023
አስተያየቶች የሉም
የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ
ጥቅምት 28, 2023
አስተያየቶች የሉም