12. የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማኅበር ዓላማዎች ምንድን ናቸው?

nty

ሰኔ 29, 2023

የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ፤

የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ እና ሕጋዊ ተፈጻሚነት እንዲጠናከር ለማድረግ ባለመብቶች የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ማስተባበር እና የመንግሥትን ጥረት ማገዝ፤

የሀገሪቱ የቅጅና ተዛማጅ ኢንዱስትሪ ሕግና ሥርዓትን በተከተለ መልኩ እንዲጎለብት ማድረግ እና የባለመብቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤

የአባላቱን መብትና ጥቅም በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት ማስጠበቅ፣ ማልማትና ማሳደግ፡

የኪነ-ጥበብ እና የሥነ-ጥበብ ዘርፍን በመደገፍ እና በማልማት ለሀገር ዕድገት የሚያበረክተውን አስተዋፆ ማሳደግ፡፡

ከላይ ከተገለጹት ዓላማዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሌሎች ተግባራትን ወቅት በጠበቀ ሁኔታ መፈጸም፡፡